የጉራጌ ዞን ተፈጥሯዊ መስህቦች
የጉራጌ ዞን ተፈጥሯዊ መስህቦች
የጉራጌ ብሔር እንደሌሎቹ የሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የአኩሪ ባህል ባለቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር ለዘመናት በአብሮነት ሲኖር በፈጠረው የህይወት መስተጋብር ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶችንም ለሀገራችን አበርክቷል፡፡ የዚህ ፅሁፍ አላማም ጉራጌ በዘመናት የህይወት ዑደቱ በማህበራዊና ባህላዊ ህይወቱ ያቆያቸው ባህላዊ እሴቶቹን፣ታሪካዊ ቅርሶቹ፣ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ሁነቶቹ ይዳስስበታል፡፡
ጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ

በ2003 ዓ.ም የተካለለው ጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ ከሀገራችን ብሄራዊ ፓርኮች አንዱ ሲሆን መገኛው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን ውስጥ ነው፡፡ የፓርኩ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 360 ኪሎ ሜትር ስኬር ሲሆን በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ / ከአበሽጌ፣ ከቸሃ እና ከእኖር ወረዳ/ የተወጣጡ በአጠቃላይ 24 ቀበሌያት ያጎራብቱታል፡፡ ፓርኩ ከመዲናችን አዲስ አበባ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ 178 ኪ.ሜ እና ከዞኑ ዋና ከተማ ወልቂጤ 20 ኪ.ሜ ይገኛል፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች መካከል ለመዲናችን አዲስ አበባ በጣም በቅርበት የሚገኝ ብሔራዊ ፓርክ ያደርገዋል፡፡

ጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ በ2003ዓ.ም ከተመሰረቱ ብሄራዊ ፓርኮች አንዱ ሲሆን የሚገኘውም በጉራጌ ዞን ነው፡፡ የፓርኩ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 360 ኪሎ ሜትር ስ£ር ሲሆን በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ /የአበሽጌ፣የቸሃ እና የእነሞርናኤነር ወረዳ/ በአጠቃላይ 24 ቀበሌያት ያጎራብቱታል፡፡ ፓርኩ ከመዲናችን አዲስ አበባ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ 178 ኪ.ሜ እና ከዞኑ ዋና ከተማ ወልቂጤ 20ኪ.ሜ ያገኙታል፡፡በዚህም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች መካከል ለመዲናችን አዲስ አበባ በጣም በቅርበት የሚገኝ ብሔራዊ ፓርክ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም ብሔራዊ ፓርኩን ከአዲስ አበባ የሰዓታት ጉዞ በማድረግ መጎብኘት የሚቻል ሲሆን ከባህር ወለል በላይ /Altitude 1060-1835 /ሜትር ዓመታዊ የዝናብ መጠን/Rainfall/ 960-1400ሚ.ሜ፣ የአየር ንብረት/Climate/ ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ አጭር የዝናብ ወቅትና ከሰኔ እስከ መስከረም ወር ረጅም የዝናብ ወቅት ሲሆን ከጥቅምት እስከ መጋቢት ደግሞ የሙቀት ወቅት ነው፡፡ ከሰኔ እስከ ነሀሴ ያሉት ወራቶችም ዳግም ቀዝቃዛ ነው፡፡ብሔራዊ ፓርኩ ስያሜውን ያገኘው ከጊቤ ወንዝና ሸለቆ መነሻ አድርጎ ነው፡፡ በብ/ፓርኩ ውስጥ ሙሉ ቀን በርካታ ወንዞች ያለማቋረጥ ቁልቁል ይወረወራሉ፡፡ የሉቄ ፍል ውሃ ፓርኩን ለየት ካደረጉት ገፅታዎች አንዱ ሲሆን ከ30-50 የሚደርሱ የፍል ውሃ ምንጮች ቦታቸውን ጠብቀው ያለማቋረጥ ይፍለቀለቃሉ፡፡ ዳጎሳ ፏፏቴ፣አቾ ፏፏቴ ፣ቃሽቃሽየ ፏፏቴ፣ደርኪ ፏፏቴ ቁልቁል ሲወረወሩ ከሚያስተጋቡት ድምፅ ጋር ተዳምሮ ተፈጥሮውን ይበልጥ ያደምቁታል፡፡ የአካባቢው የእፅዋት እንጨት ከቁጥቋጦ ደን የሚመደብ ሆኖ የተለያዩ የግራር ዝርያዎች አባሎ፣ቀውጥ፣ቦቶሮ፣ጋምብሎ፣የእጣን ዛፍና ሌሎች በርካታ የእፅዋት ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡ እንዲሁምአንበሳ፣አጋዘን፣ድኩላ፣ዘንዶ፣ነብር፣፣ከርከሮ፣የዱርአሳማ፣ጉማሬ፣ዝንጀሮ፣ጦጣ፣ጉሬዛ፣ፌቆ፣አዞ፣ሽኮኮ፣አልድጌሻ፣ዱፋርሳ የመሳሰሉት የዱር እንስሳት መኖሪያ ነው፡፡
አረቅጥ ሀይቅ

በጉራጌ ዞን በርካታ ታሪካዊ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም የጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ፣በርካታ ዋሻዎች፣ገዳማት፣መስጂዶች ፍል ውሃዎችና ፏፏቴዋች ተፈጥሮአዊ ደኖች እንዲሁም ሀይቆች ባለቤት ነው፡፡ እነዚህ የቱሪዝም ሀብቶች በየአመቱ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ይጎበኟቸዋል፡፡የአረቅጥ ሀይቅ በጉራጌ ዞን በአረቅጥ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ይገኛል፡፡ ሀይቁ ከአረቅጥ ከተማ በስተ ሰሜን ምስራቅ በ1 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡በተንጣለለ መሬት ላይ የሚገኘው የአረቅጥ ሀይቅ ከወልቂጤ ከተማ በ68 ኪሎ ሜትር ከአዲስ አበባ 219 ኪሎ ሜትር ርቀት ይገኛል፡፡ሀይቁ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለአሳ ምርት፣ለመዝናኛም ያገለግላል።134.5 ሄ/ር ላይ ተንጣሎ ሚገኘው ሀይቁ አማካኝ ጥልቀቱም 2-5 ሜትር እንደሚደርስ ይገመታል።
ይህ ሀይቅ ከወልቂጤ ወደ ሆሳዕና በሚወስደው የአስፋልት መንገድ በቅርብ ርቀት ከመገኘቱም በላይ በክረምት ውሃው ሙልት ብሎ በዙሪያው ለአይን ማራኪ በሆኑ የጉራጌ ባህላዊ ቤቶች እና የአረንጓዴ ልማት ታጅቦና በተለያዩ የአእዋፋት ዝማሬዎች ታክሎበት ለቱሪስት ምቹና አስተማማኝ ስፍራም ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪነትም ሀይቁ ዳር ላይ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ሙሉወርቅ ሎጅ ለቦታው ልዩ ውበትን አላብሶታል።በበጋ ወራትም የሀይቁ መጠን የመቀነስ ሁኔታ አይታይበትም በዚህ ሀይቅ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ዳክዎችና የተለያዩ የአእዋፋት ዝርያዎች በውሃው ተንሳፈው ሲታዩ ልዩ ውበቶች ናቸዉ ፡፡
ወገፐቻ ጥብቅ ደን

ወገፐቻ ጥብቅ ደን(ዛራ ) በጉራጌ ዞን ጔታ ወረዳ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ የሰየመው የቀበሌ ስም ነው፡፡ እዚህ ቀበሌ ላይ ውብ የተፈጥሮ ስጦታ ይገኛል የዛራ ተፈጥሮአዊ ደን ከ 29 ሄክታር በላይ ስፋት ያለው ሲሆን ሀገር በቀል እጽዋቶች ጽድ ፣ዝግባ ፣ ሾላ፣ኮሶ እና ሌሎችም ዛፎች በብዛት ይገኙበታል፡፡እድሜያቸዉ እስከ 250 ዓመት የሚደርሱ ጥቅጥቅ ዛፎች በውስጡ አቅፎ የያዘ ውብ የተፈጥሮ ገጸ በረከት ነው፡፡በአሁኑ ሰዓት ደኑ በአካባቢው ማህበረሰብና በሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ሲሆን በደኑም ዉስጥ ጦጣዎች፣ጉሬዛዎች፣የተለያዩ የአእዋፍ ዝርያዎች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ሌላዉ በእዚሁ ደን ዉስጥ በቀደምት ጊዜያት የተለያዩ የጎሳ መሪዎች ሹመት ማፅደቂያ ቦታና ተቀምጠዉ ንግስናቸዉ የሚፀድቅበት “ኧርጉስ ኧምሬ” የሚባሉ ድንጋዮች በደኑ ዉስጥ ይገኛሉ፡፡ዛራ በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ የሰየመው የቀበሌ ስም ነው፡፡ እዚህ ቀበሌ ላይ ውብ የተፈጥሮ ስጦታ ይገኛል፡፡ የዛራ ተፈጥሮአዊ ደን፡፡ ደኑ ከ4 ሄክታር በላይ ስፋት ያለው ሲሆን ሀገር በቀል እጽዋቶች ጽዶች፣ዝግባዎች ፣ሾላዎች፣ኮሶዎችና ሌሎችም ዛፎች በብዛት ይገኙበታል፡፡ እድሜያቸዉ እስከ 250 ዓመት የሚደርሱ ጥቅጥቅ ዛፎች በውስጡ አቅፎ የያዘ ውብ የተፈጥሮ ገጸ በረከት ነው፡፡ታዲያ ደኑ ከተፈጥሮአዊ ይዘቱ ባሻገር ታሪካዊ ዳራም አለው፡፡ በየዓመቱ በታህሳስ ወር በቀን ሃሙስ የሚከበር ታላቅ “”የጭሽት በዓል”” አለ፡፡ ይህ በዓል የጌታ ዋቅ(ማንድወ) የሚባል ባህላዊ አምልኮ ነው፡፡ የአምልኮዉ መሪ የዛራ ደማም በመባል ይታወቃሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት እየቀረ የመጣ ቢሆንም በየአመቱ ጭሽቱ ሲከበር ሁሉም የአካባቢው ነዋሪ የፈረሰ ጉግስ ትዕይንት ያከናውኑ እንደነበር የታሪክ አባቶች ምስክነታቸውን ይሰጣሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ደኑ በአካባቢው ማህበረሰብና በሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ሲሆን በደኑም ዉስጥ ጦጣዎች፣ጉሬዛዎች፣የተለያዩ የአእዋፍ ዝርያዎች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ሌላዉ በዚሁ ደን ዉስጥ በቀደምት ጊዜያት የተለያዩ የጎሳ መሪዎች ሹመት ማፅደቂያ ቦታና ተቀምጠዉ ንግስናቸዉ የሚፀድቅበት “ኧርጉስ ኧምሬ” የሚባሉ ድንጋዮች በደኑ ዉስጥ ይገኛሉ፡፡
ቆጠር ገድራ ደን እና ታሪካዊ ዋሻ

የቆጠር ገድራ ደን በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ልዩ ስሙ ቆጠር ገድራ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ጥብቅ ደን ነው:: የቆጠር ገድራ ቀበሌ እንዲሁም የደኑ ስያሜ ያገኘው በአከባቢው ከሚገኘው የቆጠር ጎሳና በወቅቱ አከባቢውን ሸፍኖ ከነበረው ገድራ /አስታ/ ቁጥቋጦ ነው፡፡ ገድራ በአሁኑ ወቅት ጠፍቷል በሚባል ደረጃ ላይ ያለና በድሮ ዘመን በተለይ በማይታረስ መሬት ላይ በስፋት ይገኝ የነበረው የአስታ /ቁጥቋጦ/ የጉራጊኛ ስምነው፡፡ የቆጠር ገድራ ደን መነሻ ከጥንት ጀምሮ በጎሳው ተከብሮ ይጠበቅ ስለነበረ ከአስታው በተጨማሪ የተለያዩ ሀገር በቀል ዛፎች እየበቀሉና እየተስፋፉ በመጠቀል ደኑ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በሀበሻ ጽድ እየተሸፈነ ሊመጣ ችሏል፡፡የቆጠር ገድራ ደን ባሁኑ ወቅት ጠቅላላ ስፋቱ 320 ሄ/ር ሲሆን ከማንኛውም ዓይነት ንክኪ ውጭ ሆኖ ህብረተሰቡም የደኑን የልማት ባለውለታነት በመገንዘብ ልክ እንደ ዓይኑ ብሌን ጥበቃና እንክብካቤ ያደርግለታል፡፡ ማለትም ከዚህ ደን ዛፍ መቁረጥ ቀርቶ የወደቀው ዛፍ እንኳ ያለ አካባቢው ነዋሪ እውቅና እንዳይነሳ ቃለ መሃላ በመግባት ከውስጥም ሆነ ከውጪ ደን ጨፍጫፊዎች እየተከላከለው ይገኛል፡፡ የቆጠር ገድራ ደን ችፍግ ጥቅጥቅ ብሎ ከሩቅ ለሚመለከተው በባለሙያ የተከረከመ እሰከሚመስል ድረስ ተፈጥሮ ራሱ ከርክሞ ለአከባቢው ልዩ ውበትና ግርማ ሞገስ አላብሶት ይገኛል፡፡ የቆጠር ገድራ ደን በ2003 ዓ.ም በ6ኛው መቶ ክፍለዘመን እንደነበሩ የተነገረላቸውና በውስጣቸው በርካታ ኃይማኖታዊ ቅርሶችን የያዘው የቆጠር ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም እና በርካታ የተለያዩ ዋሻዎች አምቆ የያዘ ደን ነው። እነዚህ ዋሻዎች በሀይማኖታዊ አገልግሎት ይጠቀሙበት እንደነበር እና አሁንም አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። ከነዚህ ዋሻዎች 7ቱ ለጎብኚዎች ክፍት ናቸዉ። እንግዲህ ክቡራን አንባቢዎቻችን ይህንን ውብ ስፍራ ለመጎብኘት ሲመጡ እንደ አትርፎ ጊዮርጊስ ካቴድራል ፣ ትረር ፏፏቴ ፣ዲር መስጂድ ታሪካዊ ጀፎሮዎች ሌሎች በርካታ መስህቦች መጎብኘት ይችላሉ።
ዓርባን ዋሻ በወፍ !!

በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከሚገኙ ተፈጥሯዊ ከሆነ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ የዓርባ Audubon Russellvilleን ዋሻ አንዱ ነው። እድሜ ጠገብ ደኖች፣ ዋሻዎች፣የሀይማኖት ተቋማት፣ ፍልውሃና ፏፏቴዎች በወረዳው የሚገኙ የቱሪስት መስህቦች ሲሆን ለዛሬ በወረዳው ጎምራ ቀበሌ የሚገኘውን ተፍጥሯዊ ዓርባን ዋሻ የምናስቃኛቹ ይሆናል።የአርባን ዋሻ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጎምራ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የሚገኝ ተፈጥሯዊ ዋሻ ሲሆን ከመዲናችን አዲስ አበባ በ145 ኪ.ሜ ሲገኝ ከወረዳችን ዋና ከተማ ከመሃል አምባ በ22 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።አርባን ዋሻ ተፈጥሯዊ ሲሆን በወንዝ ዳርቻ የሚገኝና የዋሸው ሰው መግቢያ በር 5 ሜትር ርዝመት ያለውና የውስጥ ክፍሉ ከመሬት 2·2 ሜትር ከፍታ ሲኖረው የውስጥ ለውስጥ ርዝመቱ ከ85 ሜትር በላይ ሲረዝም የጎኑ ስፋት ደግሞ ከ20—30 ሜትር ስፋት ያለው ማረኪ ዋሻ በመሆኑም በዞናችን በቁመቱም በስፋቱም እንዲሁም በርዝመቱም ትላልቅ ከሚባሉ ዋሻዎች አንዱ ነው።በዋሻው ዙሪያ የተለያዩ የዱር እንሰሳትና አዕዋፈት ተሽቆጥቁጦ ልዩ ውበትን የተጎናፀፈ ነው ።ይህ ዋሻ ለተለያዩ የምርምር ስራዎች በተለይም ለአርኪዮሎጂ አጥኚዎች ምቹ ሲሆን የአርኪዮሎጂ ባለሙያዎች ቢያጠኑት ተጨማሪ ግኝቶች ማግኘት እንድሚችሉ መገመት ይቻላል። በተጨማሪም ስፍራው ለቱሪስቶች ምቹና ሳቢ የቱሪዝም መዳረሻ በመሆኑ ሁሉም ወደዚህ ድንቅ ተፍጥሯዊ ስፍራ በመምጣት መንፈስዎንና አእምሮዎትን አድሰው ይመለሳሉ ይምጡና ይጎብኙ ይዝናኑ።
ጀፎረ/ባህላዊ አውራ መንገድ/

በጉራጌ ህይወት ጀፎረ/አውራ መንገድ /ልዩ ታሪክ አለው፡፡ ለጉራጌ ጀፎረ ሁሉም ነገር ነው፡፡ አገልግሎቱም ሁለገብ ነው፡፡ ለጉራጌ መንደሮች ትልቅ ውበት መላበስ ምክንያቱ ባህላዊ የቤት አሰራሩና አሰፋፈሩ ብቻ ሳይሆን ከዘመኑ መሀንዲስ ቅየሳ የማይተናነሰው በመንደሮቹ መሀል ለመሃል የሚያልፈው ግርማ ሞገስ የተላበሰው ባህላዊ አውራ መንገድ ነው፡፡በጉራጌ ታሪክ ጥንት መሬት የሚከፋፈለው በባህሉ በተመረጡ አባቶች/የዥርዳነ/የመሬት ልኬት ዳኞች አማካኝነት ስለነበር /ጀፎረ/ባህላዊ አውራ መንገድ ልኬት ቅድሚያ ይሰጠው የነበረ ሲሆን የጎን ስፋቱ እስከ 100 ሜትር ሲሆን መስቀልኛ መንገዶች በሚያልፉበት እስከ 150 ሜትር ስፋት ሲኖራቸው ርዝመቱ ግን በመሀል የሚያልፍ ወንዝ ገደል ወይም ደን እስከሌለ ሳይቋረጥ ይቀጥላል፡፡በጉራጌ ባህል/ጀፎረ/ ለባህላዊ አውራ መንገድ/ የተቀመጠን መሬት አጥሮ ወደ ግል ግቢ መከለል በምንም መንገድ የተወገዘ ነው፡፡ በጉራጌ የጀፎረ ፋይዳ በጥቂቱ፡-
ማህበራዊ ክንውኖች ሁሉ የሚከናወኑበት፣
ሰው ሲሞት የለቅሶ ስርዓት የሚከናወነው በጀፎረ ነው፡፡ እግረኛ እና ፈረሰኛ ሙሾ የሚደረድረውና ኦታሞ እየተመታ የሚለቀሰው በዚሁ ጀፎረ ነው፣
ሰርግ ሲኖር የሙሽራውና የሙሽሪት አጀቦችና ወገኖች በዘፈን ግጥም የሚሞጋገሱትና በሽማግሌዎች የሚባረኩበት ፣ ሙሽሮች አጋጌጣቸው የሚታይበትና ውበታቸው ጎልቶ የሚወጣበት በእናቶችና በአባቶች የሚመረቁበት፣
ህፃናቶች የሚቦርቁበት፣ጎረምሶች የገና ጨዋታ የሚጫወቱበት፣ ዳመራ የሚቃጠልበት፣ ወጣቶች ፈረስ ጉግስ የሚለማመዱበት፣በቅሎና ፈረስ የሚገራበት፣ኮርማዎች እርስ በርሳቸው አቅማቸውን የሚፈትሹበትና የሚያጓሩበት፣ከብቶች የሚውሉበትና የሚጠበቁበት፣ ሽማግሌዎች ስለማህበራዊ ህይወታቸውና አጠቃላይ ኑሮአቸው በጋራ የሚመክሩበት ፣ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት የሚከናወንበት ፣ መንገደኛ ያለ አንዳች ችግር የሚጓዝበት ነው፡፡
ፋይዳው እጅግ ብዙ የሆነው የጉራጌ ህዝብ ባህላዊ እሴት በዓለም ቅርስነትም ተመዝግቦ እውቅና እንዲሰጠው ያስፈልጋል፡፡
የጉራጌ ማህበረሰብ ባህላዊ የምሕንድስና ጥበብ

ጉራጌዎችን ታታሪ ጥበበኛ ከሚያሰኟቸው ነገሮች ውስጥ የመንደር አቀያየሳቸውና የሳር ቤት አሠራራቸው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ ማራኪ የመንደር ገጽታ እንዲኖራቸው ከጥንት ጊዜ ጀምረው የሚታወቁበት የምሕንድስና ጥበብ አስደማሚ ነው። ‹‹ጀፎረ›› ይባላል፡፡በጉራጌኛ ‹‹ጀፎረ›› ማለት አውራ መንገድ ማለት ነው፡፡ ጀፎረ ከመሠረታዊ ጠቀሜታው ባለፈ ለጉራጌ መንደሮች ውበትን በማላበስ የጎላ አስተዋጽኦ አለው፡፡በጉራጌ የመንደር አመሠራረት ያለ ጀፎረ አይታሰብም፡፡ ጀፎረ አረንጓዴ ሳር የለበሰ እና በሁለት ትይዩ መንደርተኞች መካከል የሚገኝ ሰፊና ማራኪ አውራ መንገድ ነው፡፡ ለአካባቢው ነዋሪዎች መግቢያና መውጫ እንዲሁም መተላለፊያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ እስከ 60 ሜትር ድረስ ስፋት ያለው ይኽ የወል መንገድ ከመንገድነት ባሻገር ለተለያዩ ማኅበራዊ ኩነቶች ያገለግላል፡፡
ጀፎረ ለማኅበረሰቡ እንደሠርግ ያሉ የደስታ፣ እንደለቅሶ ያሉ የሐዘን ማኅበራዊ ሥነ ሥርዓቶች መከወኛ ስፍራም ነው፡፡በሠርግ ወቅት ሰርገኞች የሚጨፍሩበት፣ አባቶችና እናቶች እንዲሁም የሰፈር አዛውንቶች ልጆቻቸውን መርቀው የሚሰጡበት ቦታ ነው፤ ጀፎረ፡፡ከዚህም በተጨማሪ ጀፎረ የለተለያዩ ስብሰባዎች፣ እንደ ፈረስ ጉግስና መሰል ባህላዊ ትዕይንቶች የሚካሄዱበትም ነው፡፡ የጉራጌ እረኞች ከብቶቻቸውን የሚያመላልሱበት በዚሁ ጀፎረ በተባለው የወል ስፍራ ነው፡፡በጉራጌ ባህል ጀፎረ ወይም ባህላዊ አውራ መንገድን አጥሮ ወደ ግል ማካለል የተወገዘ ተግባር ነው፡፡ ነውር ነው። ይህን ስርዓት ተላላልፎ የተገኘ ግለሰብ ቢኖር በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያጣል፡፡ ከማንኛውም ማኅበራዊ ግንኙነት ይገለላል፡፡በጉራጌዎች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበረው የመስቀል በዓል በዚህ የወል ስፍራ ላይ ነው የሚከወነው፡፡ በበዓሉ ልጃገረዶችና ጎረምሶች ከደመራው ሥነ ሥርዓት በኋላ ባህላዊ ጨዋታዎችን የሚጫወቱበት ስፍራም ነው፤ ጀፎረ፡፡ጉራጌ ጀፎረን መቀየስ የጀመረው ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት እንደሆነ የአካባቢው የዕድሜ ባለጸጎች ያስረዳሉ፡፡
የጀዳ ተራራ

ይህ የምትመለከቱት ተራራ የጀዳ ተራራ ተብሎ ይጠራል። የሚገኘው በጉራጌ ዞን በእነሞርና እንደጋኝ
ወረዳዎች ድንበር ላይ ነው። አንድ ጎኑ እነሞር ፣ ሌላ ጎኑ ደግሞ የእንደጋኝ ወረዳዎች በባለቤትነት የያዙት ሲሆን ፣ ወዲያኛው ጫፍ ደግሞ ጌቶ ወረዳ ድንበር ድረስ የተዘረጋና ውብትን ከጅቦች መንጋ ጋር አቅፎ የያዘ ተራራ ነው ጀዳ።
የአዝጋተር ፏፏቴ
